Add Your Heading Text Here

መልአከ ምክሩ ቅዱስ ሚካኤል ጽዋ ማኅበር

ኑ፥ በእግዚአብሔር ደስ ይበለን፤ ለአምላክ ለመድኃኒታችን እልል እንበል።
ንዑ ንትፈሣሕ በእግዚአብሔር፤ ወንየብብ ለአምላክነ ወመድኀኒነ። መዝ. 95:1

ወንድሞች በህብረት ቢቀመጡ እነሆ መልካም ነው እነሆም ያማረ ነው :: መዝ 132 ፥ 1

ኑና ይህን ድንቅ እዩ

እግዚአብሔር ሕዝቡን አይጥላቸውም፤ የምድር ዳርቻዎችም በእጁ ውስጥ ናቸው፥ የተራሮች ከፍታዎች የእርሱ ናቸው። መዝ. 95፡ 4

በጽዋ ማህበሩ እስከ አሁን የተሰሩ ስራዎች

እርሰዎም የዚህ በረከት ተሣታፊ ለመሆን ከፈሉ ያግኙን፣ ወይንም በገንዘብ ለመርዳት የሚከተልውን ይጫኑ

ጽዋ ማኅበር ትውፊታዊ አመጣጡ እና ሥራዐቱ

የጽዋ ማኅበር ትውፊታዊ አመጣጡ እና ሥራዐቱ እንዴት እንደሆነ ለመገንዘብ የሚከተለውን ይጫኑ

መልአከ ምክሩ ቅዱስ ሚካኤል ጽዋ ማኅበር

M.M. St. Michael Tswa

ማህበር፡ የሚለው፡ ቃል፡ ሲተረጎም፡ በአንድነት፡ በመተባበር፡ መኖር፡ ማለት፡ ሲሆን፡ ቃሉ፡ የግዕዝ፡ ቃል፡ ነው። በማያያዝም፡ በምድራዊው፡ ዓለም፡ በማህበር፡ ወይም፡ በመተባበር፡ መኖር፡ የተጀመረው፡ ከቀዳሚዎቹ፡ ፍጥረታት፡ ከአባታችን፡ ከአዳምና፡ ከእናታችን፡ ከሔዋን፡ ጊዜ፡ ጀምሮ፡ እንደሆነ፡ እና፡ ከዚያም፡ በኋላ፡ ልጆቻቸውና፡ የልጅ፡ ልጆቻቸው፡ አሁን፡ እኛ፡ እስካለንበት፡ ዘመን፡ ድረስ፡ በተለያየ፡ መልኩ፡ ሲጠቀሙበት፡ እንደቆዩ፡ እና፡አሁንም፡ እየተጠቀሙበት፡ መሆኑን፡ ለቃውንተ፡ ቤተክርስቲያን፡ በሰፊው፡ ያስረዳሉ።

ጽዋ

ጽዋዕ ማለት በቁሙ ኩባያ’ዋንጫ’የመጠጥ መሣሪያ የሚል ትርጉም አለው፡፡ በሌላም በኩል በጽዋ ተቀድቶ የሚሰጥም መጠጥ ጽዋ ይባላል፡፡ ማኅበር ማለት ደግሞ‹‹ኀብረ›› አንድ ሆነ ከሚለው የግእዝ ቃል የወጣ ነው፡፡ በአንድ ላይም ጽዋ ማኅበር ማለት በጽዋ ለመጠጣት የሚሰባሰቡ የምእመናን አንድነት ማለት ነው፡፡ ጽዋ ማኅበር ምእመናን በወር ወር ተራቸውን እየጠበቁ እየደገሱ የሚያበሉበት እንዲሁም ችግረኞችን የሚረዱበት ሥርዓት ነው፡፡ በጽዋ ማኅበር መሳተፍ በረከትን ያሰጣል (መዝ 3.8′ ምሳ10.7) እንዲሁም በማቴ 10.42 ላይ እንደተገለጸው ዋጋን አያጠፋም፡፡

ማኅበሩ በጌታችን’በእመቤታችን’በቅዱሳን መላእክት’በጻድቃንና በሰማዕታት ዕለት በቤተክርስቲያን ዙሪያ ወይም በምዕመናኑ ቤት የሚካሄድ ነው፡፡ ማኅበርተኖቹም ከእኅትና ከወንድምነት ባለፈ እርስ በእርሳቸው በጋብቻ መተሳሰር የለባቸውም፡፡ የአንድ ጽዋ ማኅበር አባላት ብዛት አሥራ ሁለት መሆን አለበት፡፡ ምክንያቱም በዓመት ውስጥ ያሉት ወራት አሥራ ሁለት በመሆናቸው ሁሉም አባል ተራው እንዲደርሰው ነው፡፡ ከአሥራ ሁለት በላይ ከሆኑ ግን ድርብ/ደባል/ በሚባለው አከፋፈል መሰረት በወር ውስጥ ሁለት ወይም ከዚያ በላይ ሆነው በመመደብ ተራቸውን እንዲያወጡ
ይደረጋል፡፡

የጽዋ ማኅበር አመሰራረት ትውፊታዊ ባህልን የተከተለ ነው፡፡ በዘመነ ሥጋዌ የመጀመሪያዎቹ ክርስቲያኖች በአንድነት የፍቅር ማዕድ /አጋፔ/ ይመገቡ ነበር፡፡ ኋላም ቅዱሳን ሐዋርያት ከጌታ እርገት በኋላ ካመኑና ከተጠመቁ ክርስቲያኖች ጋር በአንድነት ኑሯቸውን እንዳደረጉ መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል፡፡ ሐዋ.ሥራ 2.44-47 
በዘመነ ሰማዕታት ግን ይህ ሁኔታ በአብዛኞቹ   ክርስቲያኖች ተረስቶ ነበር፡፡ በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ግን ይህ ትውፊት በአባቶታቻችን ጸሎት’ብርታት ባህሉ ወጉ ሥርዓቱ ሳይፋለስ ተጠብቆ ለትውልድ ትውልድ ሲተላለፍ ቆይቷል፡፡ የቤተክርስቲያን ታሪክ እንደሚነግረን በኢትዮጲያ የመጀመሪያው የጽዋ ማኅበር መሥራች አቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን ሲሆኑ ወቅቱም በ330 ዓ.ም በአክሱም ነበር፡፡ የማሕበሩ ስም በመጀመሪያ ‹‹ማኅበረ ጽዮን›› ይባል የነበረ ሲሆን ቆይቶ ‹‹ማኅበረ ጽዮን ሰማያዊ›› ተባለ በመጨረሻም ‹‹ጽዮን ማርያም›› በመባል ስሙ ሊለወጥ ችሏል፡፡ በ14ኛው መ/ክ/ዘ አፄ ዘርዓያዕቆብ ሕዝቡን በሃይማኖቱ የበለጠ ለማጽናት በማሰብ በቅዱሳንና በእመቤታችን ስም ማኅበር እንዲጠጣ ሕግ አወጡ፡፡ ቀጥሎም
በ16ኛው መ/ክ/ዘ ማኅበረ ሰላም መድኃኔዓለም የተባለ በአቡነ መብዓጽዮን የተቋቋመ ማኅበር እንደነበር የቤተክርስቲያን ታሪክ ይነግረናል፡፡

“የሚያስተውል እግዚአብሔርንም የሚፈልግ እንዳለ ያይ ዘንድ እግዚአብሔር ከሰማይ የሰው ልጆችን ተመለከተ።" መዝ. 53:2

There are projects we are supporting. Please donate and be part of this mission.

Upcoming Events & Announcements

Consequuntur Magni Dolores Eos

Lorem ipsum dolor sit amet, consectetur adipiscing elit, sed do eiusmod tempor incididunt ut labore et dolore magna aliqua. Ut enim ad minim.

Consequuntur Magni Dolores Eos

Lorem ipsum dolor sit amet, consectetur adipiscing elit, sed do eiusmod tempor incididunt ut labore et dolore magna aliqua. Ut enim ad minim.

Consequuntur Magni Dolores Eos

Lorem ipsum dolor sit amet, consectetur adipiscing elit, sed do eiusmod tempor incididunt ut labore et dolore magna aliqua. Ut enim ad minim.

How Does It Feel To Help

Get In Touch With us

Name Here